በስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በክቡር አቶ ዘይኔ ቢልካ የተመራው የዞኑ አስተባባሪ አካላት በግንባታ ላይ ያለውን የወራቤ ከተማ የውስጥ ለውስጥ አስፋልት መንገድ አሁናዊ የስራ እንቅስቃሴን ተመለከቱ።
በስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በክቡር አቶ ዘይኔ ቢልካ የተመራው የዞኑ አስተባባሪ አካላት በግንባታ ላይ ያለውን የወራቤ ከተማ የውስጥ ለውስጥ አስፋልት መንገድ አሁናዊ የስራ እንቅስቃሴን ተመለከቱ።
ወራቤ፣ የካቲት 4/2018
የስልጤ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የህዝብ ግንኙነት
__________________________________________
በስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በሆኑት በክቡር አቶ ዘይኔ ቢልካ የተመራው የዞኑ አስተባባሪ አካላትና ሌሎች የስራ ሀላፊዎች በህብረተሰብ ተሳትፎ እየተገነባ የሚገኘውን የወራቤ ከተማ የውስጥ ለውስጥ የአስፋልት መንገድ አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ ተመልክተዋል።
ከ 1 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ በማህበረሰብ ተሳትፎ እየተገነባ የሚገኘው አስፋልት የ 5 ነጥብ 73 ኪሎ ሜትር ርዝመትና 18 ሜትር የጎን ስፋት ያለው ሲሆን የከተማዋን ቁልፍ አከባቢዎች በማስተሳሰር ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎችን ከማሳለጥ ባሻገር የከተማዋን ሁለንተዊ ገጽታ በመቀየር ተወዳዳሪነቷን እንደሚያሳድግ ታምኖበታል።
የዞኑ አስተባባሪ አካላት የፕሮጀክቱን አሁናዊ አፈጻጸም በተመለከተበት ወቅት ግንባታው ፈጥኖ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆን የዞንና የከተማ አስተዳደር ባለድርሻ አካላት የሚያደርጉትን ድጋፍና ክትትል አጠናክረው እንዲቀጥሉ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
በማህበረሰብ ተሳትፎ እየተገነባ የሚገኛው የአስፋልት መንገድ ግንባታ 1 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር ያህሉ የመጨረሻ ዙር አስፋልት በመልበስ ላይ መሆኑንና በቅርብ ቀናት ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን በጉብኝቱ ወቅት ተገልጿል።
በመስክ ምልከታው ላይ የስልጤ ዞን ዋና የመንግስት ተጠሪና የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ዋና ሀላፊ ክብርት ወ/ሮ ነዒማ ሙኒር፣ የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪና ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙበራ ከማል ፣ ረዳት የመንግስት ተጠሪና የፖለቲካና የርዕዮተ አለም ዘርፍ ሀላፊ አቶ ሁሴን ሱነሞ፣ ረዳት የመንግስት ተጠሪና የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ሳሊያ ሀሰን፣ የወራቤ ከተማ ዋና ከንቲባ አቶ ያሲን ከሊል እና ሌሎች የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።